top of page

ዕውቀትና ግንዛቤ

በሥራ የሚተረጎምና በቀጥታ ኑሮን ማሳደግ የሚያስችሉ የትምህርት ዘርፎች የዕድገት መሰረት ናቸው


4ኢፕር የትምህርት ፕሮግራም የተመሠረተዉ በአሁኑ ጊዜ አስቸኳይና በስራ ላይ ዉሎ ሕዝቡ ምርቱን በየስራ መስኩ እንዲያጎለምስ የሚያስችለዉ ሙያና ዕዉቀት እንዲጨብጥ ማድረግ ነዉ፡፡ ከማንኛዉም በበለጠ ቅድሚያ የሚሠጠዉ የሠዉ ልጆች በተፈጥሮ የተሰጣቸዉን የማሰብና የፈጠራ ጸጋ በስራ ላይ እንዲያዉሉት ቁልፉን የሚከፍት ግንዛቤ ማሰራጨት ማሳደግ ነዉ፡፡ ግንዛቤዉ ከተያዘ ማንኛዉም ሰዉ በተቀላጠፈ መንገድ በመረጠዉና ይቀናኛል ብሎ ባሰበዉ የስራ መስክ ሙያዉን ተምሮ ምርቱን ማጎልመስ ይችላል፡፡

ሁሉም ሰው የግንዛቤው ደረጃ ከፍ ቢደረግና አስፈልጊውን ዕውቀት ቢያገኝ የተሻሻለ ኑሮ(ያለዕርዳታ) መኖር ይችላል

ግንዛቤያቸው ካደግ  መመኘት፤ ማለም፤ የበለጠ በመትጋት ያማረ ሕይወት ሊኖራቸው ይችላል

የትምህርት ፕሮግራሙ

3 ዋና መስመሮች

  1. ሕዝቡን ሊደርሱበትና በራሳቸዉ ጥረት ሊሠሩትና ሊቀዳጁት የአማረ የኑሮ ዓይነት ማሳየትና ግንዛቤአቸዉ ዉስጥ እንዲያስገቡ ማድረግ። በግንዛቤአቸዉ ዉስጥ ከገባ ሊመኙ ሊያልሙት ዕቅድ አዉጥተው በስራ ሊተረጉሙት ይችላሉ፡፡ ከግንዛቤዉ ጋር ልዩ ልዩ የኢኮኖሚ ዕድገት ፕሮግራሞች ይዘት በማሳወቅ በመረጡት የሥራ ዘርፍ ቀልጣፋ ሙያ በአጭር ጊዜ እየተማሩ ወደምርቱ አለም እንዲሰማሩ ማገዝ፡፡ ኢንዱስትሪ ለሚሰሩት መሳሪያዎችን እንዴት እንደሚያንቀሳቅሱ ፋብሪካዎች ዉስጥ ደረጃ በደረጃ የሚደረጉት ሥራዎች እንዴት እንደሚሠሩ የዘመናዊ ግብርናንና አግሮ ኢንዱስትሪ እንዴት እንደሚሰሩ ቀልጣፋ ትምህርት ሠጥቶ ሥራ ማስጀመር ቅድመ ትምህርት መጨረስ አያስፈልጉትም። በተለይም በብዙ ሚሊዮን የሚሠማራበት የግንባታ ስራ ስለ ጥንቃቄ ቅድመ ገለጻ ከተሰጠው ሕዝቡ በቀላሉ የሚገነዘበዉና የሚያሳድገዉ ሙያ ነዉ፡፡

  2. በስራና በልዩ ልዩ ሙያ ለተሠማሩት ዕዉቀታቸዉን እንዲያዳብሩ ብሎም በአለም ዙሪያ አዲስ ጥበብ ፈጠራ ላይ በሚደረገዉ ዉድድር ተሳታፊ እንዲሆኑ ማነሳሳትና መንገዱን ማስተካከል፡፡

  3. ወደ ፊት አገራቸዉን ሕዛባቸውን በልዩ ልዩ ጥልቅ የሙያ መስመር ለማገልገል ለሚፈልጉ የከፋተኛ ትምህርት ዕድል እንዲኖራቸዉ ይህንንም መስመር መዘርጋት ቀጣይነት ያለዉ ምርምርና ፈጠራ ለሰዉ ልጆች ዕድገት ዋና መሠረት ስለሆነ ፋላጎት እንዲያድር ምክርንና ድጋፍን መስጠት፡፤

አስፈላጊውን ዕውቀትና ግንዛቤ ካገኘ 

ማንኛውም ሰው ጤናማና ሰላማዊ ኑሮ መኖር የሚያስችለው አምርቶ ሊኖር ይችላል።    ግንዛቤን ማሳደግና በተሰማራበት መስክ አስፈላጊውን

ዕውቀት ማስተላለፍ ተቀዳሚ ተግባር ነው።

bottom of page