top of page
አማርኛ መነሻ ገጽ

በመሀንዲሳዊ ዘዴ የተቃኘ ሁሉን አቀፍ ዘላቂ ልማት

ተባብሮ በመስራት ወደላቀ
ብሩህ የኑሮ እድገት

በቅርብ የወጡ

እንኳን ደህና መጡ

 

እንደ ኢትዮጽያ ያሉ አገሮች በራሳቸው ጥረት በአጭር ጊዜ ውስጥ ምርታቸውን ማጐልመስ ወደ ዘመናዊ ጤናማና ሰላማዊ ኑሮ መሸጋገሪያ ዘዴ በዚህ ድሕረ ገጽ ቀርቧል፡፡ 4ኢፒር /4EPR/ ተብሎ የቀረበው የአሠራር መንገድ እውቀትንና ግንዛቤን በማሳደግ ኢኮኖሚና ምጣኔ  ኃብትን በማሳደግ የተፈጥሮ ሐብትን በመንከባከብና በማለምለም የተመሠረተና በመሐንዲሳዊ አሠራር የተዋቀረ ምርት ማጐልመሻ ሥነ ምግባር ነው፡፡ በዚህ ዓይነት ስኬትና አጠራር የተሰዬመበት ደግሞ ሦስቱን የሕብረተሰብ ዋና ችግሮች ከሥረ መሠረቶቻቸው ነቅሎ ለመጣል ነወ፡፡

ሦስቱ ዋና ወጥመዶች የእውቀት ማነስ፣ ድሕነትና የተፈጥሮ አካባቢ መላሸቅ ናቸው፡፡

  Scroll Down OR Use አማርኛ Anchor Menu on the Top Right side  

​በቅርብ የወጡ

ለኢትዮጵያ የህብረትና

የዕድገት ጉዞ ተጨባጭ ሃሳቦች

ውድ ወገን የመኖር ዋናውና የመጨርሻው ግብ መላው ሕዝብ ከድህነት፤ ከስቃይ፤ ከስራ አጥነት፤ ከስደት ተርፎ የራሱን የተፈጥሮ ፀጋ በመጠቀም በመነሳትና በመተባበር እተሟላ የኑሮ ደረጃ ላይ መድረስ ነው። የትግሉ ባለቤት የሆነው ሕዝብ በሚያምናቸው ወገኖቹ፤ አስተማሪዎቹ፤ አስተባባሪዎቹ፤ መሪዎቹ፤ አማካኝነት በአጭር ጊዜ ውስጥ እግቦቹ መድረስ እንደሚችል ተገንዝቦ መሳተፍና መንቀሳቀስ አለበት። እዚህም ደረጃ ለመድረስ የሚያስችል አቅም እንዳለው አውቆ ወደፊት እንዲገፋ በዓለም ዙሪያ ያለ ወገንና ወዳጅ ሁሉ ሊተባበራቸው ይገባል

በዘር በሃይማኖት በጎሳ ሳይከፋፈል ሁሉም በአንድ ላይ ተንቀሳቅሶ በአጭር ጊዜ ሊደርስባቸው የሚቻሉ ግቦች በዚህ ድህረ ግጽ ቀርበዋል። እንዴት እንደሚተገበሩም ምዕራፍ 8 ላይ ተዘርዝረዋል።

DireDawaDam_edited.jpg

ሰውደግፍ
      ሰላም ውሃ ደስታ ግንዛቤ ፍቅር

ለቁርጠኛ ዘላቂ ልማት

ሰውደግፍ የዘላቂ ልማት መርሆዎችን መዳረሻዎች ናቸው፡፡ ​ሰላምን መሰረት አድርጎ የተነሳ ሕዝብ በጣም አጣዳፊ የሆነውን የውሃን ችግር በህብረት ጎርፎችን በመገደብ ይፈታል፡፡ ደስታን ፍቅርን ግንዛቤንም በህብረት በማዳበር ሁሉም ከስቃይና መከራ አልፎ የተሟላ ኑሮ መኖር ይችላል፡፡  ኢትዮጵያ የሚዘንበውን ዝናብ እንደወረደ ቢገደብ ሰፊ ልማት ለሚሊዮኖች፤ አዳዲስ ቀጣይ ሥራ ይፈጠራል፤ እምርታ ለውጥና ቁርጠኛ ዘላቂ ልማት ይመጣል፡፡ ሰውደግፍ መርሆአችን ይሁን፡፡

ህዝቡ ችግሮቹን በራሱ ይወጣቸዋል

ሂደቱ ቢፋጠን ስቃዩ ሁሉ ይወገዳል

ለዋናው የሕዝብ ጉዳዮች

(ድህነት፤ ስቃይ ፤ስራ አጥነት)

መፍቻ ፕሮግራሞች

በዚህ ድህረ ግጽና፤ በሰፊ ጥልቀት በሚያሳየው መጽሃፍ ቀርቧል

​መጽሐፉን በአስተማማኝ መንገድ በዚህ መድረክ ቢያዙ ይደርስዎታል። የአማርኛውን ውይነም የእንግሊዘኛውን በተመሳሳይ ዋጋ ማግኘት ይችላሉ፤ ምርጫዎን ያስትውቁ

 

የአማረኛው መጽሓፍ አዲስ አባባና ደብረ ማርቆስ ዩንቨርስቲዎች ውይይት ተካሄደብት

የአዲስ አበባውን ውይይት የሚያሳዩ 4 ቪዲዮዎችን ከዚህ በታች ይመልከቱ:-

ክፍል 1 : መግቢያና የአቶ ኢያሱ በካፋ መግለጫ

ክፍል 2 : የኢንጅነር መለሰ ተገኝ መግለጫ

ክፍል 3 : የፀሓፊው አጠቃላይ ሃሳብና ማብራሪያ

ክፍል 4 : ጥያቄና መልስ ውይይት

 

በኢትዮጵያ ዩነቨርስቲዎች የተደረጉት የ፬ኢፒር ውይይቶች ከፍተኛ ስሜት ፈጥረዋል የመተባበር መግለጫዎችም ተላልፈዋል

Thank you for your pioneering initiative bringing our country to a better stand tomorrow.

ሙሉዉን አስነብቡኝ...

የመጽህፉ ​ንባብና ቪዲዮ
በአዲስ ነገር ገጽ ይቀርባል

የመላው ህዝብ ኅብረትና ኑሮን ለማሻሻል የሚደረገ የተሳሰረ መነሳሳት በአጭር ጊዜ ችግሮችን በዘላቂነት ይደመስሣል። 

ከ40 ዓመታት በላይ የተደረገው ሂደት ህዝቡን ከድህነት አላወጣውም። 80 በመቶው አሁንም ንፁህ ውሃ፤ ኤለክትሪክ ሃይል፤ የሂወት አስፈላጊ ነገሮች የሉትም።

"ባለ ሁለት አሃዝ ዕድገት" የተባለው ማሞካሻ እንጂ በግሃድ ኢትዮጵያ ከዓለም በህዝብ ዕድገት 174ኛ ላይ ተጨፍግጋ ከመቀመጥ አላዳናትም።

ሀብታሞችም ገንዘባችሁን አታሽሹ፤ ይልቁንም ከህዝብ ጋር አብራችሁ ስሩ፤ ወታደሩም መሳሪያህን ትተህ ከህዝብ ጋር ሁሉን አቀፍ በሆነው አገርን ለማሻሻል እንቅስቃሴ ተሳተፍ። በምንም መንገድ ወገንህን አትጉዳ! አትግደል  

ለወደፊት የተወጠነው የህዝብ የዕድገት ተጨባጭ ዕቅድ ላይ መሳተፍ እስካሁን የተደረጉትን እንቅስቃሴዎች በ20 እጥፍ የሚያስከነዳ ነው። ኋላ እንዳይፀፅታችሁ በአስቸኳይ ህብረቱ ተጠናክሮ በሁሉም መስክ መሰማራት ይገባል። 

ሰላምን ለማግኝትና ከችግር ለመውጣት ዓይነተኛው መንገድ ምርትን ማሳደግ መሆኑን የሚያሳዩ አሥር ምክንያቶች

ሰዎች የማይመረጥ ምርጫ ላይ የሚደርሱት የሚሞክሩትና የሚሰሩት ሁሉ ውጤት ሳያስገኝ ነው። ህጻናትና ዕናቶች ንጹህ ያልሆነ ውሓ እየጠጡ እንደቅጠል ሲረግፉ ፤ የሚችሉትን ሁሉ ሰርተው ውጤታቸው ረሃብ ችግርና ስቃይን ማቆም ሳይችል ሲቀር፤ ሁሉን ርግፍ አርገው አገር ለቀው በርሃ ጥሰው ወደ ማይፈልጉት ወደ የማይቀበላቸው አገር ይሰደዳሉ።

ሙሉዉን አስነብቡኝ ...

GERD-Ethiopian-Dam.webp

ስለ ፬ኢፒር

ተልዕኮ

የ4ኢፒር፡- ዋና ተልዕኮ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ግንዛቤአቸዉን አሳድገዉ በልዩ ልዩ የስራ ዘርፍ ዕዉቀት ቀስመዉ ራሳቸዉን ለልዩ ልዩ የስራ መስኮች ብቁ በማድረግና በሚዘረጉት ሙያዎች ሁሉ በመሰማራት ምርታቸዉን በማጎልመስና በማሳደግ ህይወታቸዉን በተሻለና ቀጣይነት ባለዉ መንገድ እንዲመሩ መርዳት፡፡ ሙሉዉን አስነብቡኝ...

ፕሮግራሞች

በአጠቃላይ 4ኢፒር ሦስቱን ችግሮች ማስወገድ የሚቻለው ሕብረተሰቡ በተሠማራበት መስክ ሁሉ ምርተን ማጐልመስ ሲበቀና ጊዜውን በሚገባ ሲጠቀምበት ነው፡፡ 4ኢፒሪ አሠራር ምርትን ማጐልመሻ የሚሆኑ አምስት ፐሮግራሞችን አቅርቧል፡፡

  1.  የሕብረተሰቡን ግንዛቤ እውቀት ማሳደግ፣ ማስተማር

  2. ከተሞችን መሥራትና ሕዝቡ ከተማ እንዲኖር ማድረግ

  3. ኢንዱስትሪ ማስፋፋት

  4. ግብርናን በዘመናዊ መንገድ ማካሄድ

  5. የተፈጥሮ አካባቢን መጠበቅና ማለምለም

ሙሉዉን አስነብቡኝ...

10 ግቦች

በመላው አገር ለሚገኙ ህዝቦቿ የተሟላ ህይወት፤ በጤና ፤በደስታ፤ በሰላምና በፍቅር የሚኖሩባት አገር  ለመመስረት፡፡ ይህንን ለማስቻል ሁሉን ያሳተፈ፤ በብዙ ረድፎች የዳበረ፤ የእያንዳንዱን ሰው የማምረት አቅም አሁን ካለበት ከ10 እስክ 50 እጥፍ ያሳደገ፤ ቀጣይ፤ በዕውቀትና ስነምህዳሩን በመንከባከብ የተመሰረተ ሰላማዊ መርሆዎች የያዘ ታዳጊ ኢኮኖሚ በ20 አመታት ጊዜ መገንባት።  ሙሉዉን አስነብቡኝ...

ስለ ፬ኢፒር

2013

የተመሰረተበት
ዓመት

2000

የተመዘገቡ
አባላት

17

የዉይይት
መድረኮች

26

የሚድያ
ሽፋን
፬ኢ

አጋሮች

አድራሻ

Inquiries

For any inquiries, questions or commendations, please call: +16472190080 or fill out the following form

Success! Message received.

Head Office

Toronto, ON, Canada

 

team@4epr.com

Tel: +16472190080

Partnership

To apply, please send a cover letter together with your C.V. to: team@4epr.com

Connect with us
  • Facebook - Black Circle
አጋሮች
አድራሻ
bottom of page