top of page

ኢኮኖሚ

4ኢፒር - ሁሉን ያጠቃለለና ቀጣይነት ያለው የዕድገት ማጎልመሻ ያሠራር መንገድ 

መከተም

ከተማ መመሥረት 

 

ክተማ ማለት በልዩ ልዩ የስራ መስክ ተሰማርቶ ከ 50 ሺህ ሰዉ በላይ በአንድ ላይ የሚኖርበት አካባቢ ነዉ፡፡ ከተማ ዉስጥ አንደኛዉ ህዝብ የሚያመርተዉን ለሌላዉ እየተሸጠ በምትኩ አገልግሎት እየሰጠ በመረዳዳትና በመተጋገዝ በመወዳደር በሰላም ሁሉም ይኖራል፡፡

በየቦታዉ ተበታትኖ ከሚኖረዉ ከገጠሩ ሕዝብ ጋር ሲነጻጸር በከተማ የሚኖረዉ ሕዝብ የሚከተሉት ጥቅሞችን ያገኛል፡፡ 

 1. የኤሌክትሪክ ሃይል አመንጭቶ ለሰዎች በቀላል ዋጋ በአስተማማኝና ዋስትና ባለበት አይነት ማከፋፈል የሚቀናዉ አብዛኛ ሕዝብ እሚኖርበት አካባቢ ወይም ከተማ ነዉ፡፡ የከተማዉ ሰዎች መብራት አላቸዉ ልዩ ልዩ ነገሮችን በኤሌክትሪክ ሃይል ይሠራሉ፡፡

 2. ንጹህ ዉሃም በየቤቱ በቧንቧ ማቅረብ ማከፋፈል የሚቻለው ከተማ ወይም ብዙ ሕዝብ እሚገኝበት ነዉ ፡፡

 3. የመጸዳጃ አገልግሎት ከየቤቱ ያለዉን ሽንት ቤትን የመጸዳጃ ክፍል አሰባስቦ አጠቃላይ የፈሳሽ መጸዳጃ አገልግሎት የሚቀርበዉ ብዙ ተጠቃሚ ሲኖር ነዉ፡፡

 4. ትምህርት ቤቶች የጤና ጥበቃ ተቋሞች ማህበራዊ አገልግሎት መስጫ ተቋሞችንም በተሟላ መንገድ ግልጋሎታቸዉን ሊያበረክቱ የሚችሉት ብዙ ተጠቃሚ በአንድ ላይ ሲገኝ ነዉ ይህም ከተማ ነዉ፡፡

 5.  ሌሎች ልዩ ልዩ የስራና የአገልግሎት ተቆሟችንና ገብያዎችንም ማካሄድ የሚቻለዉ መግዛት መሸጥ መለዋወጥ የሚፈልግ ሕዝብ በአንድ ላይ ሲሆን ነዉ፡

ከዚህ በተጨማሪ የፈላጊና የተፈላጊ፤ ሰሪና ተጠቃሚ ህዝብ ብዛትም በአንድ አካባቢ በመኖሩ ዉድድሩና እሽቅድምድሙ የበዛ ስለሆነ አዲስ ነገር የመፍጠሩ አዲስ ዘዴ ማዉጣቱ ምርትንም ማሳደጉ ከፍተኛ ዕድል ያለበት ቦታ ነዉ፡፡

 

ኢትዮጵያ ዉስጥ ከአስራ አምስት ሺህ ሰዉ በላይ የሚኖርባቸው ከተሞች ተደምረው የተገኘው ቁጥር መቶ ሃምሳ ሲሆን የህዝብ ጠቅላላ ድምር ከ 10 ሚሊዮን በታች ነው፡፡ ይህም አሁን ከአለው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር 16 በመቶ ብቻ ነዉ፡፡ ማለትም ከ80  በምቶ በላይ የሚሆነው ህዝብ የሚኖረው ገጠር ውስጥ ነው። እንግዲህ ከተማ በምትሠጣቸው ጥቅሞች ሲመዘን የኢትዮጵያ ሕዝብ ዋና ችግር ምክንያቱ ተበታትኖ በየገጠሩ ተራርቆ መኖር ነዉ፡፡

በአንጻሩ ያደጉትና የበለጸጉት አገሮች ዉስጥ ከ80 እስከ 95 በመቶ የሚሆነዉ ሕዝብ የሚኖረዉ ከ 100ሺህ ህዝብ በላይ በሚኖርባቸዉ ከተሞች ነዉ፡፡ 

መከተም

ለገጠር ህዝብ የከተማ ኑሮ ይሻለዋል በሌላ አንጻር ሁኔታዉን ለመመርመር ከ 80 በመቶ በላይ በየትንሽ መንደሮች ተራርቆና ተበታትኖ የሚኖረዉን የኢትዮጵያ የገጠር ኗሪ ሕዝብ ሁኔታ ማስተዋል ያስፈልጋል፡፡ እያንዳንዱ ቤተሰብ ለየግሉ የሚያስፈልገዉን ነገር ሁሉ ራሱ ሠርቶ በራሱ ጥረት ይኖራል፡፡ ያኗኗር ሁኔታዎችም ይህን ይመስላሉ፡፡

 

 • የዉሃ ምንጮች ወንዞች ሩቅ ስለሆኑ በየቀኑ ሰዎች በማድጋ በጀሪካን እየቀዱ ከአንድ ሰዓት እስከ 3 ሰዓት መንገድ እየተሸከሙ ወደቤታቸዉ በማምጣት ለሚጠጡትም ለሚያበስሉበትም ያዉላሉ፡፡ ዉሃዉ ስለማይበቃ መታጠቡ እምብዛም ነዉ፡፡

 • ህጻኖችና እናቶች በከፍተኛ ቁጥር የሚሞቱት ገጠር ዉስጥ ነው የዚህም መንስኤው ንጹህ ካልሆነ ውሀ የሚመጡ በሽታዎች ነዉ፡፡ የውሃ ምንጩ ሩቅና ያልተጠበቀ በመሆኑ በቀላሉ ይበላሻል ይበከላል፡፡

 • የገጠሩ ሕዝብ የሚኖረዉ በእንጨት ጭቃ ሳር ወይም ቆርቆሮ የተሰራ ጠባብ ቤት ዉስጥ ነዉ፡፡ ማገዶዉ እንጨትና ኩበት ሲሁን ምድጃዉን መኝታዉ ተቀራራቢ በመሆኑ የሚተነፍሰዉም አየር የተበላሸ ነዉ፡፡

 • መጸዳጃ የተለየ ቦታ ስለሌለ ዉሃም በቀላሉ ስለማይገኝ ፅዳት የሚባለዉ ነገር ለተመልካች የዘገንናል ያጸይፋል

 • በአባዛኛዎች መኖሪያዎች የከብቶች በረትና የሰዎች መኖሪያም አብሮ ስለሆነ በጽዳት ለመያዝ አስቸጋሪ ነዉ፡፡

 • የግብርና ስራቸው  የሚሰሩት በጉልበታቸዉ በእንሰሳት ኃይል በማረሻና በቀንበር ነዉ፡፡

 • በእርሻና በመርህ ወራት ዝናብ ጸሐይ ዉርጭ ሳይሉ እስከ ማታ በሳምንት አምስት ቀናት ሳያወላዉሉ ይሰራሉ፡፡

 • በሳምንት አንድ ቀን ገበያ ለመሄድ ሙሉ ቀናቸዉን ያጠፋሉ፡፡ ምርታቸዉን ተሸክመዉ ወይም በከብት ጭነው ከገበያ ጨው ዘይት ልብስ ላምባ ለመብራት ገዝተዉ የመለሳሉ፡፡

 • ለዕድለኞችና ወላጆቻቸዉ ከግብርናዉና እቤት ስራ ላይ እንዲያግዙ የማያስቀራቸዉ ልጆች ትምህርት ቤቶች የሚያገኙት ለጥቂት ሰዓቶች በግር ተጉሀው ነዉ፡፡

 • የጤና መጠበቂያ ተቋሞችና ክሊኒኮች በጣም ተራርቀው ስለሚገኙ ሕዝቡ ካልታመመ አይሄድባቸውም ታሞም ሲሄድ ብዙዎች መንገድ ላይ ይሞታሉ፡፡

ከላይ የተዘረዘሩት ሁሉ ሊወገዱ ሕዝቡም ከችግር ወጥቶ የተሻለ ኑሮ ሊኖር የሚችለዉ እላይ እንደተጠቀሰዉ ሕዝቡ ከየመንደሮች ከገጠር ወጥቶ ተሰባስቦ ከተማ ዉስጥ መኖር ሲችል ነዉ፡፡ እላይ የተዘረዘሩትን የገጠር ችግሮች ለያንዳንዱ መንደር ለማዳረስ በጣም አስቸጋሪና ዉድ ቀጣይነትም የሌለዉ መንገድ ነዉ፡፡

የ4ኢፒር ከተማ ምስረታ ንድፈ ሃሳብ

 

የ4ኢፕሪ መንገድም ሕዝብ ተሰባስቦ ከተማዎችን መስርቶ በልዩ ልዩ መስክ በብዛት እያመረተ እየተለዋወጠ እየተረዳዳና እየተጋገዘ አካባቢንና ተፈጥሮን ጠብቆ መልካም ኑሮ ወዳለበት ደረጃ እንዲሸጋገር የሚያስችል መንገድ ነዉ፡፡

 1. ታጥኖ እንደሚጠብቅ እንደ ንብ ቀፎ ሁሉ የተሟሉ ከተሞች ከተሰሩ የገጠሩ ሕዝብ መጥቶ በልዩ ልዩ መስክ ተሰማርቶ ምርቱን በማሳደግ ከተሞች የተሰሩበትን ወጪ በጊዜ ሂደት ይከፍለዋል፡፡

 2. እንደ ኢሌክትሪክ የመጸዳጃ አገልግሎቶች ተሰርተዉ ለህዝቡ ቢቀርቡ እነዚህን ለማግኘት ሕዝቡ የሚያጠፋዉ የነበረዉ ጊዜ በስራ ላይ ስለሚዉል ዋጋቸውን በአጭር ጊዜ ይመለሳል፡፡

 3. በማገዶ በመጠቀም ፋንታ በተሻሉ የሀይል መስጫዎች በመጠቀም የአየርና የተፈጥሮን መበላሸት መበከልንም ማቆም ይቻላል፡፡

 4. ከተማዎች ገብቶ እያመረተና እየተደላደለ የሚኖረዉ ሕዝብ የአለም ልዩ ልዩ ድርጅቶች ምርታቸውንና ሸቀጣቸውን ሲያቀርቡ የመግዛት አቅም ይኖረዋል በአንጻሩም የኢትዮጵያን ምርት እሌሎችን ገበያ እንዲሸጥ በሩን ይከፋታል፡፡

የኢትዮጵያ መንግስት እስታክቲክስ ቢሮም ሆነ የአሜሪካ  መዝገብ (the CIA World Fact Book) የሚያሳየው የኢትዮጵያ  ብዙ ህዝብ ያላቸው 145 ከተሞች በጠቅላላ ተደምረው ያላቸው ህዝብ 10 ሚሊዮን አይሞላም.

 

ከተማ ስም                                C P 2011-07-01

አዲስ አበባ                                  2,979,100

መቀሌ                                        261,200

ናዝሬት                                       260,600

ድሬ ዳዋ                                     256,800

ጎንደር                                        227,100

አዋሳ                                         200,400

ባህር ዳር                                    170,300

ጅማ                                          143,200

ጅጅጋ                                         142,500

ደሴ                                           131,600

 

የአስሩ ታላቅ ከተሞች ድምር               4.772,800

የሚቀጥሉት መቶ ሰላሳ አምስት ድምር    4,531,700

145 ከተሞች ከ12,000 በላይ ህዝብ ድምር     9,304,500

አዲስ አበባን የሚያህሉ ክ15 እስከ 20 ከተማዎች እነማን ቢሆኑ ለአገር ጥቅም የበለጠ ይጠቅማል?

ሌሎች ተመክሮዎች


መልካም ምሳሌ

በአለፉት አስር ዓመታት እንደምሳሌና መርሆ ሆኖ የሚቀርበዉ ምሳሌ በቻይና አገር የተደረገዉ ነዉ፡፡ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ሕዝብ ወደ አዲስ እተመሠረቱ ከተማዎች በመስፈር ከድህነት ወጥቶአል ፡፡ በአሁኑ ጊዜም ቻይና ከ 300 ሚሊዮን የሚበልጥ ሕዝብ በሃያ አመታት ውስጥ ከተማ አስገብተዉ ከድህነት ለማላቀቅ ብዙ ከተማዎችን እየገነቡ ነዉ፡፤ ኢትዮጵያም ከ 10 እስከ 15 የሚቆጠሩ ከተማዎችን በሚቀጥሉት ሃያ ዓመታት ብትሠራና የገጠሩ ሕዝብ በራሱ ምርጫ እዚያ ቢኖር ድህነት ሊወገድ ይችላል፡፡

 

ብራዚልም በአልፉት ሃያ አምስት ዓመታት ባደረገችው ምርት ማሳደግ ሩጫ ከፍ ያለ ደረጃ አድርሱዋታል።

ኢንዱስትሪ ማብዛት

በጣም ተፈላጊና በብዛት ህዝብ የሚገለግልባቸውን ዕቃዎች በአገር ኢንዱስትሪ ውስጥ መስራት በጣም አስፈልጊ ነው።

ኢንዱስትሪ በትሰሩ ዕቃዎች መሳሪያዎች ማሽኖች በመጠቀም ሰዎች ስራቸውን በቀላሉ በመስራት የሚፈልጉተ በአጭር ጊዜ በማከናዎን ለመዝናናት ለመደሰት ለላ ነገር ለማድረግ  ለማረፍ የኢንዱስትሪ ውጤቶች ብዙ ጊዜ አስተርፈውላቸዋል።  በአሁን ጊዜ በአደጉ አገሮች ማንኛውም እቤትም ሆነ ሥራ ቦታ ክል እንዱስትሪ የተሰራ እቃ ና መሳሪያ የሚከናወን ነገር የለም። በአንጻሩ ደግሞ እንደ ኢትዮጵያ አሉት ታዳጊ አገሮች በገጠር መንደሮች የሚኖረው ህዝብ ጭራሽ አንድም ኢንዱስትሪ የተሰራ ዕቃ የለለበት ሞልⶆአል። ይህ የሚያመለክተው ወደ ተላደለ ኑሮ ለመጠቀም እሚደረገው ሂደት ላይ ብዙ የኢንዱስትሪ ምርት ስለሚያስፈልግ ብዙ ኢንዱስትሪ ያስፈልጋል ማለት ነው። ይህም በብዙሚሊዮን ለሚቆጠር ህዝብ የኢንዱስትሪ ሥራ ዕድል  ይፈጥራል ማለት ነው።. ይህ ሁኔታ የሚቀጥሉትን ሁኔታዎች ያሳያል

 1. የሚፈጠሩት የኢንዱስትሪ ዓይነቶችና ብዛት ብዙ እንደ መሆኑ ሁሉ የሚፈጥረዉም ዕድል አሁን ያለዉን አምስት በመቶ ወይም ሁልት ሚሊዮን በኢንዱስትሪ የሚተደዳደር ህዝብ እንደሚፈለገው ወደ ሃያ ሚሊዮን እንዲያድግ ያደርገዋል። .

 2. ይህም የህዝቡን ገቢ በብዙዕጥፍ ያሳደገዋል። ፋክተሪና ኢነዱስትሪ የሚሰሩ ስዎች በቀን እንደሙያቸው ክመቶ እስክ ሺ ብር በቀን ይከፈላቸዋል። ተመሳሳይ ምርት በማምረት የነሱን አነድ አስረኛ እንኩዋን ለሰራተኞች በከፈል ገቢያቸው በአስር እጥፍ አደገ ማለት ነው።

 3. የኢኮኖሚውን እንቅስቃሴ በኢንዱስትሪ አቅጣጫ ሲያድግ በሌሎችም ረድፎች አብሮ ይመጥቃል። ንግዱ የአገልግሎት ሰጭ ተቅዋሞች በእጥፍ ድርብ ያድጋል 

 4. በማንኛውም አገር ክ 80% እስከ 90% የሚሆነው የኢኮኖሚ ዕንቅስቃሴ የሚካሄደው እዚያው አገር ውስጥ ነው። ይህም አንዱ ያመረተውን ለላው እየገዛው ስለሆነነው።.   

 5. ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን ጥሬ ዕቃ በበቂ ለማቅረብ የሚደረገው ጥድፊያም አያሌ የስራዕድል ይፈጥራል.

 6. ኢኮኖሚው ካደገ ኢንዱስትሪዎች የተገዙበትን ብድርም በቀላሉ መክፈል ይቻላል.

ኢንዱስትሪ
ኢንዱስትሪ የሚያስፈልግብት ምክንያቶች


የኢንዱስትሪ አስገላጊነት ፫ ምክንያቶች

 1. ያለ ኢንዱስትሪ መስፋፋት መሰረታዊ የሆነ የኢኮኖሚን የህብረተሰብ የኑሮ እድገት መደረስ አይቻልም። 80% የሆነውን የኢትዮጵያ ህዝብ ወደኢንዱስትሪን ወደ ትባባሪ የአገልግሎት ዘርፎች ካልተሸጋገረ ክችግር ሊወጣ አይቻልም

 2. ማሽኖች የማምረቻ መሳሪያዎች ልዩልዩ በኢንዱስትሪ የተሰሩ መገልገያዎች የሚሰሩ ኢንዱስትሪ ገብቶ ካልተመሰረተ የህዝቡ የምርት ቅልጥፍና ሊሻሻል አይጭልም። ኢንዱስትሪዎች አገር ውስጥ ከተስፋፉ ህዝቡም ለስራ ተገቶ ይነሳሳል። .

 3. የኢንዱስትሪ ምርትን ለ80 ሚሊዮን ህዝብ ማዳረስ የሚቻለው እቃዎችን በማስመጣት ፋንታ ኢንዱስትሪዎች አገር ውስጥ ሲገቡ ነው። ይህም የስራ መፍጠሪያ ዋና መሰረት ነው።

 

በ4ኢፒር አስተሳሰብ የሚከተሉት አምስት መደባዊ ኢንዱስትሪዎች በቀደምትነት ያስፈልጋሉ

 1. ምርት ለማጎልመስ የሚያስችሉ መሳሪያዎች ማሽኖች ሞተሮች የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች

 2. የአገሪትዋን ተቅዋሞችና መሰረቶች ለመስራት የሚያስችሉ ምሳሪያዎችና ዕቃዎች የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች 

 3. ትላልቅ ከተማዎች ለመስራት የሚያስችሉ ኢንዱስትሪዎች

 4. የግብርና ውጤቶችን በተሻሻለ ደረጃ አዘጋጀተው የሚያቀርቡ ፋብሪክዎች

 5. ህዝቡ በየእለቱ የምኢጠቀምባቸውን አስፈልጊ ቁሳቁሶች የሚያመርቱ ኢንዱስትሪዎች

ግብርና

ግብርናን ዘመናዊ ማድረግ

ግብርናን በዘመናዊ መንገድ ማሻሻል ከፍተኛ ቦታና ቅድሚያ የሚሰጠዉ ፕሮግራም ነዉ፡፡ ይህም የሆነበት ማክንያት የግብርና አመራረት ዘዴ ከፍተኛ መሻሻል የሚያስፈልገዉ ጉዳይ ነዉ፡፡ ምንም እንኳን ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነዉ የኢትዮጵያ ሕዝብ በግብርና የተሰማራ ቢሆን ዉጤቱ ግን በአገር ዉስጥ ያለዉን የምግብ ፍላጎት እንኳን ሊያሞላ አልቻለም፡፡ ዘመናዊ የግብርና ዘዴዎች በስራ ላይ ከዋሉ በልዩ ልዩ የማምረቻ መሳሪያዎች እየታገዙ ጥቂት ሕዝቦች ለአገሪቱ የሚያስፈልጋት ከማሟላት ተርፈዉ ለሌሎች የሚተርፍ ምርት ማምረት ይችላል፡፡ ጥቂት ሰዎች (እንደበለጸጉት አገሮች ከ10 በመቶ የጠቅላላዉ አገር ሕዝብ) የሚያመርቱት ለግብርናዉ የኢኮኖሚ መስክ ሙሉ እንቅስቃሴና ዉጤት በቂ ኃይል ነዉ፡፡ ይህ ማለት 75 በመቶ የሚሆነዉ ሕዝብ እርሻዉን ትቶ ወደ ሌሎች የኢኮኖሚ ዘርፎች መሰማራት አለበት ማለት ነዉ፡፡ የግብርና ኢኮኖሚዉ በአጠቃላይ በሶስት ረድፎች መሻሻል ይገባዋል፡፡

 1. እያንዳንዱ የገበሬ ቤተሰብ ለየግሉ በሁሉ ዓይነት የግብርና ዘርፍ ጥረት ከሚያደርግ ምርት በዕጥፍ ድርብ እንዲበዛ በተወሰነ ምርት ላይ ማተኮር አለበት፡፡ ይህም ማለት አንድ ገበሬ ቤት በጎች ዶሮዎች ላሞችና እርሻዉም አብሮ ከሚካሄድ አንደኛዉ ላይ ትኩረት ሰጥቶ ያንን በጥራትና በብዛት ቢያመርት የበለጠ ትርፍና ገቢ ይኖረዋል ማለት ነዉ፡፡ በተለይም ደግሞ ተባብረዉና ተደራጅተዉ የእህል አምራቾች፤ የስጋ አምራቾች፤ የዶሮ አምራቾች ሆነዉ ቢደራጁና የማምረቻ የማከፋፈያ ዘዴዎችና መዋቅሮች በሕብረት ቢገዙ ምርታቸዉ የበለጠ ይጎለምሳል ማለት ነዉ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ አመራረት የተትረፈረፈ ምግብ ለማምረት ይረዳል፡፡ እጥረትን ያቆማል የዋጋ ንረትን ያቆማል ሕዝቡም የተሟላ ምግብ አግኝቶ ጤናማ ህይወት በመኖር ከችግር ይገላገላል፡፡

 2. ከብቶችም በማርባት ላይ የተሰማሩት በከብቶች መኖ ዉሃ እና ጤና ላይ በማተኮር በዘመናዊ ቴክኖሎጂ በመታገዝ ከከብቶች የሥጋና የወተት ዉጤታቸዉን በብዙ እጥፍ እንዲያድግ ይሆናል፡፡ ይህ ዓይነት አሰራር አላግባብ እየተጋጡ የሚሸረሸሩት የዕርሻ መሬቶች እንዲጠበቁ ያደርጋል፡፡ ከብቶች በቂ መኖ በቂ ዉሃ ሳያገኙየሚንከራተቱበት ሂደት ይቆማል፡፡ 

 3. የእህል ምርትም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በጥራትና በይዘት በቴክኖሎጂ ታግዞ ብዙ ድካም በሌለበት ሁኔታ በብዛት ይመረታል፡፡

 4.  ኢትዮጵያ ዉስጥ በየክፍለ ሀገሩ በተፈጥሮ በቅለዉ ሰዉ ሳይለቅማቸዉ እየወደቁና እየበሰበሱ የሚጠፉትን እንደ ማንጎ፤አቮካዶ፤ሙዝና የመሳሰሉት ፍራፍሬዎችን በሚገባ ማዳበርና ወደ ገበያ እንዲቀርቡ መደረግ ይገባዋል፡፡ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በዓለም ገበያ የፍራፍሬ ዋጋ እየናረ በመጣበት ጊዜ ኢትዮጵያ ዉስጥም ችግር ባለበት ወቅት ፍሬዎችን ማዳበርና በሚገባ መንከባከብ ከፍተኛ የገቢ ምንጭ ይሆናል፡፤

 5.  በከብት እርባታ ላይ ብቻ ተወስነዉ እንደ ወቅቱ ከብቶቻቸዉን ተከትለዉ ከቦታ ቦታ ሲንከራተቱ የሚኖሩት ህዝቦች በዘመናዊ መንገድ የከብት ርባታ በማደራጀት የተሟላና መንከራተት የሌለበት ከፍተኛ ዉጤት ያለዉ ኑሮ እንዲኖሩ መደረግ ይገባዋል፡፡

 6. ተመሳሳይ የስራ ዓይነቶች በየክፍለ ሀገሩ ቢካሄዱም አንደኛዉ ክፍለ ሃገር ከሌላዉ የተለየ አስተዋጽኦ ቅድሚያና ጠቃሚ ቦታ እየተሰጠዉ በመለዋወጥና በመረዳዳት በመተጋገዝ ሁሉም በአንድ ላይ የሚያድጉበት መንገድ በመከተል የሁሉም ሕዝብ የኑሮ ደረጃ የሚያድግበትን መንገድ መከተል ያስፈልጋል፡፡

 7. ለግብርናዉ የኢኮኖሚ መስክ ማደግ ዋናዉ መንገድ አሁን ያለዉ ሕብረተሰብ ወደ ኢንዱስትሪ ወደ ግንባታ፤ ንግድና የመሳሰሉት የአገልግሎት መስጫ የስራ መስኮች በፈቃደኝነት ሊሰማራ ነዉ፡፡ እነዚህ ሰዎች ሁሉ የማምረት ችሎታቸዉ በማደጉ የሚያገኙትም ገቢ በመጨመሩ የግብርና ምርቶችንም የመግዛት አቅማቸው ይጨምራል፡፡ የግብርና ዉጤት አይነትና ጥራትም በአስተማማኝና በአኩሪ ደረጃ ያድጋል፡፡

 8. ለማጠቃለልም የግብርና ፕሮግራም ዋና ዋና ግቦች የሚከተሉት ናቸዉ፡፡

 • በብዙ እጥፍ የግብርና ምርት ማሳደግ ለዚህም ዘመናዊና የተፈጥሮ መንገዶችን በስራ ማዋል፡፡ ለአገር ዉስጥ በሙሉ የሚበቃ ማምረት ትርፍንም ለዉጭ መሸጥ ዉጤቶች/ዕድሎች የምርት መጎልመስና ብዙ ገንዘብ ማግኘት የተለዩና ጥራት ያላቸዉ ሰብሎች ማምረት ሰፋ ያለም ምርጫ ማምረት የተመላ ኑሮ መኖር

 • አግሮ ኢንዱስትሪዎችን በስራ ላይ በማዋል የሚመረቱት ምርቶች ለሕዝብ በበለጠ ተሻሽለዉና ተሰናድተው እንዲቀርቡ ማድረግ ፡፡በአጭር ጊዜ እንዳይበላሹ መንከባከብ

 • በግብርና የተሰማሩት ሰዎች ገቢ በሌላ ስራ ላይ ከተሰማሩት ጋር እንዲመጣጠን ማበረታታት

 • ብልሽትና ጥፋት እንዲቀንስ ወይም እንዲጠፋ ቀጣይነትና የሚታደሱ የሐይል መስጫዎችንና ዕቃዎችን መጠቀም፡፡ 

ግብርና
bottom of page