top of page

ስለ ፬ኢፒር

ስለ ፬ኢፒር
ተልዕኮ

የ4ኢፒር፡- ዋና ተልዕኮ የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ ግንዛቤአቸዉን አሳድገዉ በልዩ ልዩ የስራ ዘርፍ ዕዉቀት ቀስመዉ ራሳቸዉን ለልዩ ልዩ የስራ መስኮች ብቁ በማድረግና በሚዘረጉት ሙያዎች ሁሉ በመሰማራት ምርታቸዉን በማጎልመስና በማሳደግ ህይወታቸዉን በተሻለና ቀጣይነት ባለዉ መንገድ እንዲመሩ መርዳት፡፡

ተግባሮች

 

  1. ሕብረተሰቡን እራሱን እንዴት ማሻሻል እንደሚቻል ለማንኛዉም ሰዉ በየትኛዉም አገር ስለአለባቸዉ ዕድሎች ስለማምረቻ መሳሪያዎችና ምርትን እንዴት ማጎልመስ እንደሚቻል ማሳየት ስለ ፕሮጋራሞችና ስለልዩ ልዩ የዕድገት ዘርፎችና ተሞክሮዎች ግንዛቤያቸዉን ማሳደግ ፡፡ ለሰዉ ዘር በሙሉ በተፈጥሮ የተሰጠዉን የፈጠራ ችሎታና ጸጋ እንዲጠቀሙበትና በስራ ላይ እንዲያዉሉት ማነቃቃትና ማበረታታት፤ብሎም የራሳቸዉን የወገኖቻቸዉን የአገራቸዉን ከዚያም የዓለምን ችግሮች ለመዘከር/ለመቅረፍ እሚደረገዉ እንቅስቃሴ ላይ እንዲሳተፉ መርዳት፡፡

  2. ኢትዮጵያ ዉስጥ ያለዉ ችግርና ድህነት ለማስወገድ ለሚደረጉት ጥረቶች አማራጭና ደጋፊ ፕሮግራሞች ማቅረብ፤የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ በአገርቤትና በዉጭ አገር የሚገኙ ከነጓደኞቻቸዉና ከደጋፊዎቻቸዉ ጋር በመሆን ሊሳተፉበት የሚችሉበትን ከፍተኛ ዉጤት የሚያስገኙ ፕሮግራሞችን ዉጥን ከመጀመሪያዉ እስከ መጨረሻዉ በዝርዝር ማቅረብ፤ በዉጤቱም ድርብ ድል ማለትም ችግርን ማስወገድና አካባቢን ከጥፋት ማዳን ግቦችን እንዲጎናጸፉ መርሆዎችን እየተከታተሉ መርዳት፡፡

  3. በሕብረተሰቡ ላይ በተረጋጋሚ እየተከሰተ ብዙ ነፍስና ኃብት ለሚያመጣዉ የተፈጥሮ ክስተት (እንደ ድርቅ ያሉ) ህዝቡ በያለበት በብዛት አምርቶ በመቆጠብ ከችግሮች በቀላሉ እንዲድኑ መርዳት ፡፡

  4. አካባቢን የተፈጥሮ ይዘት እየቦረቦሩና እያጠፉ የሚገኙትን ድርጊቶች የተሻለ መፍትሔ በምትክነት በማቅረብ ድርጊቶችን ማቆም ፡፡ እነዚህ ድርጊቶች ዛፎችን ቆርጦ ለማገዶ ጫካዎችን በመመንጠር ለእርሻ መሬትን ጎርፍ እንዳይሸረሽር የሚያደርግ አስተራረስ የመሳሰሉት ይገኙበታል፡፡ መፍትሔዎች ለመሻት ከሀገር ዉስጥና ከአለም አቀፍ የተፈጥሮ አካባቢ ጠባቂና ተቆርቆሪ ቡድኖች ጋር አብሮ መስራት፡፡

5. ፕሮግራሞችን በትክክል ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ የሚያስፈልጉ መሳሪያዎችን ዕቃዎች ኢንዱስትሪዉችና ሌሎችንም ወጪዎች የሚሸፍን ገንዘብ ከኢንቬስተሮችና ከተለያዩ የገንዘብ ምንጮች ማሰባሰብ ለሚሰበሰበዉም ገንዘብም ሆነ ኢንዱስትሪ ለባለቤቶች ከተወሰነ ዓመታት በኀላ ዋናቸዉ ከአጥጋቢ ትርፍ ወይም ወለድ ጋር እንዲመለስላቸዉ ማስተማመኛ መስጠት። 

ፕሮግራሞች
ፕሮግራሞች
1
2
3
4

የህብረተሰቡን ግንዛቤና ዕዉቀት ማሳደግ

በተራራቁ መንደሮችን ገጠሮች ለሚኖረው አብዛኛዉ ሕዝብ ስለተሻለ የአኗኗር ዓይነት ፤ ምርታቸዉን አሳድገዉ ሊያገኙትና ሊደርሱበት እንደሚችሉ ግንዛቤአቸዉን ማሳደግ ፤ የሰዉ ልጆች በተፈጥሮ ያላቸዉ የማስተዋል የማሰብና የፈጠራ ችሎታ በአግባቡ ከተቀሰቀሰ ከፍተኛ ዉጤት ያመጣል፡፡

ዋናዉ ተልዕኮ ህብረተሰቡን በራሳቸዉ ጥረት ዘመናዊ ቤት እየኖሩ ለራሳቸዉ እና ለልጆቻቸዉ ጤናማ የደስታ ህይወት እንደሚኖራቸዉ ቢያዉቁ ሁልጊዜ በማሰብ በመመኘት ታትረዉ ለመስራት ይነሳሳሉ ወደ ሌላ የስራ ዘርፍ ወደግንባታ ሥራ ወደ ኢንዱስትሪና በቴክኖሎጂ ለመጠቀምና ምርት ለማብዛት በከፍተኛ ጉጉት ይነሳሉ፡፡ ሙሉዉን አስነብቡኝ

እንከትም፣ ከተሞችን እናብዛ

አሁን ያሉትን ትንንሽ ከተሞችና መንደሮች አጣመርን በተጨማሪም አመቺና ተስማሚ በሆኑ ቦታዎች ላይ ከ አስራአምስትእስከ ሃያ በእቅድ የተመዘገቡ ታላላቅ ከተማዎችን እንገንባ፡፡ በዓለም ውስጥ የተሻሻሉ አገሮች ውስጥ ከ8ዐ በመቶ በላይ የሚሆነው ሕዝብ የሚኖረው በከተማ ነው፡፡ በአንጻሩ ኢትዮጽያ ውስጥ ከተማ ቀመስ አካባቢዎች ውስጥ የሚኖረው ህዝብ 2ዐ በመቶ ብቻ ነው፡፡

ሕዝቦች በታላላቅ ከተሞች ውስጥ መኖር ያለባቸው በሚከተሉት ዋና ምክንያቶች ነው፡፡

  • የሕዝቡን መሠረታዊ አገልግሎቶችን፣ ማለትም እንደ ውሃ፣ ኤሌክትሪክ ኃይል፣ የፈሳሽ አገልግሎት፣ ትምህርት ቤትና የጤና አገልግሎት በቀልጣፋና በአነስተኛ ወጪ ለብዙ ሕዝብ ማዳረስ የሚቻለው፡ ከተማ ሲሆን ነው፡፡ እነዚህ አገልግሎቶች በተናጥል ለሚገኙ መንደሮችና ትናንሽ ከተሞች ለማዳረስ አዳጋችና ከፍተኛ ወጭ እንደሚያስፈልግ ግልጽ ነው፡፡

  • በትልልቅ ከተሞች የተለያዩ የተሰባጠሩ ተደጋጋፊ የሆኑ የሥራ፣ የአገልግሎት፣ የሙያና የንግድ እንቅስቃሌዎች ስላሉ ሰዎች በሚቀናቸው የሥራ መልክ ተሰልፈው የበለጠ በማምረት ከፍተኛ ገቢ ስለሚያገኙ ከገጠሩ አኗኗር እጅግ በጣም ያማረ ኑሮ መኖር ይችላሉ፡፡

ስለዚህ ትልልቅ ከተማዎችን በመቆርቆር የገጠሩ ሕዝብ ወደ ከተማ ገብቶ የበለጠ በማምረት ኑሮውን ያሻሽል፡፡ ሙሉዉን አስነብቡኝ

 

ኢንዱስትሪ እናስፋፋ

በሀሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ኢንዱስትሪዎችን እናቋቁም የኢንዱስትሪዎች መቋቋም ለብዙ ሕዝብ የሥራ እድል ይከፍታል፡፡ የኢንዱስትሪዎችም አብዥዘኛው ምርት አሊያም ምርቱ በሙሉ አገር ውስጥ ተፈላጊ ነው፡፡ በአሁኑ ጊዜ የመግዛት አቅሙ ስለሌለው ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው የኢትዮጽየ ሕዝብ ኢንዱስትሪ በተሠሩ እቃዎች አይገለገልም፡፡ ምርቱን ሲያዳብር ገቢውም ሲጨምር የተሻለ ኑሮ ለመኖር የኢንዱስትሪ ምርቶች በሰፊው ስለሚፈልግ አገር ውስጥ መሠራቱ ጥቅሙ እጥፍ ድርብ ነው፡፡

ልዩ ልዩ መሣሪያዎች፣ የቤት እቃዎች፣ መድኃኒቶች፣ ኬሚካሎች፡ ፐላስቲኮች፣ የሕንጻ እቃዎች፣ የኤሌክትሮኒክስ እቃዋችና ሌሎችም ለብዙ ሚሊዮን ሕዝብ የሚበቃ  ይፈለጋል፡፡ ይህ ዓይነቱ ፍላጐት ሊዳረስ የሚችለው አገር ውስጥ ሲሠሩ ነው፡፡ ይህም በአሁኑ ጊዜ 5 በመቶ ብቻ በኢንዱስትሪ ሥራ የተሰማራውን የኢትዮጽያ ሕዝብ ቁጥር ወደ 30 በመቶ ሊያሳድገውና እንደአደጉት አገሮች ሕዝብ የስራ ስምሪት ደረጃ ሊያሳድግ ይችላል፡፡

ሙሉዉን አስነብቡኝ

 

ግብርናን ዘመናዊ እናድርግ

​በአብዛኛዎች የለሙ አገሮች ውስጥ በግብርና ሥራ ተሰማርቶ የሚገኘው ሕዝባቸው በቁጥር ከአስር ከመቶ በታች ነው፡፡ እነዚህ ከአንድ አስረኛ በታች የሆኑ አምራቾች የሚያመርቱት ከአገራቸው አልፎ የዓለም ገብያን ያጥለቀልቃል፡፡ በኢትዮጵያ ውስጥ ከ8ዐ በመቶ በላይ በግብርና የተሰማራው ሕዝብ የሚያመርተው ግን ለአገሩ ሕዝብ አልበቃ ብሎ በየጊዜው የምግብ ችግርና የምግብ ዋጋ ንረት እያስከተለ ይገኛል፡፡ ይህም የሆነው የኢትዮጵያ የአየር ጠባይ በዓመት ሦስት ጊዜ ሰብል ማስገኘቱ እየታወቀ ብሎም መሬቱ ለምነቱ እየታወቀ ነው፡፡

5

ዋናው ምክንያቱ ግን ባልተሻሻለ መሣሪያና ጊዜ ባለፈበት ዘዴ በመጠቀም ነው፡፡ ሕዝቡ ወደ ከተማ ለመግባት እድሉ ቢኖረው በተለያዩ የሥራ መስኮች ቢሠማራ ጥቂቶች ቀርተው ግብርናውን በዘመናዊ መሣሪያና በተሻሻለ መንገድ ሊያካሄዱና በቂ ሊያመርቱ ይችላሉ ማለት ነው፡፡የ4ኢፒአር ግብርናን በዘመናዊ መንገድ ማሻሻል ሁለት ዓቢይ መርሆዎችን የያዘ ነው፡፡ ለዘመናት አባቶች ለልጅ ልጅ ያስተላለፉት የእንስሳትና እጽዋት እድገት ልምድን በመመርኮዝ ዘመናዊ ብልሃቶችንና መሣሪያዎች መጠቀም ናቸው፡፡

ሙሉዉን አስነብቡኝ

የተፈጥሮ ሃብትና አካባቢ መጠበቅ፤

አካባቢን መጠበቅ መንከባከብ 

በየ አመቱ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ዛፎች ለማገዶ ያለምትክ እየተቆጠረ ይገኛሉ፡፡ የእርሻንም መሬት ለመጨመር ጫካዎች እየተመነጠሩ የመሬት ሽፋን እየተገፈፈ ይገኛል፡፡ ግልጽ የሆነዉ መሬትም ጠራራ ጸሐይ ነፋስና ዝናብ ሲያርፍበት እየተሸረሸረ ለም አፈር እየተጠረገ በመሄዱ መሬቱ እየደረቀ ነዉ፡፡ ይህንን ሂደት በአስቸኳይ ማቆም ለህብረተሰቡ ህልዉና ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ ነዉ፡፡

እየተቆረጠ  ማገዶ የሚሆነዉ ዛፍ የሚፈጥረዉ የካርቦን ጭስ ተጠራቅሞ ጠፈርን እያበላሸ ይገኛል፡፡ ዛፎችን ጫካዎችን የካርቦን ጭስ ማጣሪያ መሆናቸዉን በመጥፋቱ የአየር ጠባይ መበከል ዓለምን እየጎዳ ይገኛል፡፡

ለማገዶ የተለያዩ የሃይል ማመንጮዎችን በመጠቀም ግብርናም በዘመናዊ መንገድ ቢካሄድ የዛፎችን መቆረጥ ያቆመዋል ለዚህም የዓለምን ድጋፍና ትብብር ያስገኛል፡፡ 

ሙሉዉን አስነብቡኝ

አላማ

አላማ

  • ትምህርት - የህዝቡን ግንዛቤ ማሳደግ, ፈጣን የሙያ ሥልጠና አክሂዶ ህዝቡ ሥራ እንዲይዝ ማበረታታት. ሰዎች የማያውቁት ልዩ ስጦታቸውን እንዲጠቀሙበት ማበረታታት 

  • ​ኢኮኖሚ (ድህነት ማጥፋት) - የገጠር ሰዎች በራሳቸው አነሳሽነት ከተማ ገብተው በልዩልዩ የሥራ መስኮች ተሰማርቶ የበለጠ በማምረት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ መንገዱን ማስተካከል.

  • አካባቢ- የተፈጥሮ አካባቢን በመገባ በመጠበቅ አሁንም ለወደፊት ትውልድም እንዲጠቅም ማድረግ. ዛፎቸን ያለምትክ መጨፍጨፍን በማቆም የመሬቱን ማንሰራራት መሻት፤ የካርቦን ግዝም የሚያመጣውን ጉዳት መቀነስ ማቆም።  

  • መሓንዲሳዊ- ሁሉም ፕሮግራሞች ተጨባጭ ተደግሞ በሰራ ውጤቱ አንድ ዓይነት የሆነ ውጤት የሚያመጣ ሳይንሳዊ አሰራር ነው።.ፕሮግራሙ የሚመለከታቸው፤ በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ የሚነካቸው ሁሉ ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ ድረስ በልዩልዩ መንገድ እየተሳተፉና አስተውጽኦ እያደረጉ ፕሮግራሙን እንዲንከባከቡ ማስተባበሪያ መርሆ መስጠት። . 

  • ምርት ማጎልመስ - ሕዝቡን ከችግር በራሳቸው ጥረት እንዲወጡ የሚቻለው፡ ብዙ ማምረት በሃቱን ሲማሩ፤ ቀልጣፋ ሥራ  መሥራት ሲለምዱ፤ የቴክኖሎጂ መሳሪያ ሴቀሙ ነው። የቀን ከፍያቸውና የሚያመርቱት በቀን አንድ ዶላር በአስር እጥፍ ማደግ ይችላል።

የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረት

የኢትዮጵያ ህዝብ ትኩረት የሚሠጣቸዉ ኢላማዎች/ግቦች 

በለፉት ሃያ ዘመናት በአለም ላይ የሰዉ ላጆች ታምራዊ የፍልስፍና ዉጤቶች በማግኘትና በስራ ላይ በማዋል ያልታሰቡና አስደናቂ የኑሮ ዕምርታ እንዲኖረን ረድተዋል፡፡እነዚህ ከዚህ ቀደም ያልተደረጉት ዕምርታዎች እንደ ኢንትርኔት የኮምፒዩተር በማናቸዉም የሰዉ የዕለት ጉዳይ ላይ መዋል የሞባይል ስልክ፤ ኢሜልና ቪዲዮ ፤ በአለም ዙሪያ መሰራጨት ቀደምት ቦታ ይዘዋል፡፡

እነዚህ ሂደቶችና ግስጋሴዎች የሚያሳዩት ታላላቆቹና አስቸጋሪ የሆኑ እንደ ድህነት ኋላቀርነት፤የጤና ጥበቃ አለመሟላት የመሳሰሉት የአለም ጉዳዮች ሁሉ መፍትሄ የሚያገኙበት ጊዜ መቃረቡን ያሳያል፡፡ ከዚህም በመነሳት እንደ 4ኢፒር ያሉ ፕሮግራሞች ተዘርግተዉ ስነ ምግባሮች በየቤቱ ከተሰራጨ ህዝቡ በአንድ ላይ ተነስቶና ተባብሮ የተፈጥሮ ሃብቶችን በሚገባ ስራ ላይ በማዋል ከባለሙያዎችና ከዓለም አቀፍ ኢንቬስተሮች ጋር በመተባበር በሚመጡት ሃያ ዓመታት የሚከተሉት ግቦች ሊደርስ ይችላል፡፡ (The total investment for 4EPR will not be as much as what was spent in Iraq or Afghanistan, but it will definitely transition 80 million Ethiopians into a better standard of living, curb environmental degradation, and also pay back all the investment with reasonable rate of return and big thank you.)

  1. ማንኛዉም ቤተሰብ የኤሌትሪክ ሃይል፤ የቧንቧ ዉሃ፤ ዘመናዊ የተመሏ ማዕድ ቤት ከነማቀዝቀዣዉ ማብሰያ ያለበት ቤት ዉስጥ መኖር ይችላል፡፡ እንደ አደጉት አገሮች ምግቡንም በቅርቡ ካለ ግሮሰሪ በመግዛት ቀልጣፋ ኑሮ መኖር ይችላል፡፡ የኤሌትሪክ ሃይል ዉሃ መብራት መጸዳጃ አገልግሎትም በየቤቱ በአስተማማኝ በተመጣጠነ ዋጋ ቀርቦለት ተጠቃሚ ሆኖ ይኖራል፡፡

  2. ማንኛዉም ሰዉ በስራ ተሰማርቶ በሚያገኘዉ ገቢ በተራ ቁጥር አንድ ለሚያስፈልጉት ወጭዎች ከከፈለ በኋላ በሚተርፈዉ ደግሞ ሌሎች ነገሮችን አሟልቶ ከዚያም ለመጦሪያና ለድንገተኛ ቀን ተቀማጭ ቆጥቦ በደስታና በጤና ይኖራል፡፡ አገሪቷም ከህዝብ በሚሰባሰበዉ የታክስ ገንዘብ መልካም አስተዳደር ከመስጠት አልፎ ለድንገተኛ አደጋም የሚሆን በቂ ንብረት ይኖራታል፡፡

  3. የሁሉንም ሰዉ ጤንነት የሚንከባከበዉ የጤና አገልግሎት አገር ዉስጥ በሙሉ በመስፋፋት ማንኛዉም ሰዉ በቅርቡ በሚገኝ የጤና ተቋም ይገለገላል፡፡ ከዚያም በተጨማሪ የመዝናኛ ቦታዎች የሃይማኖት ተቋሞች በያሉበት ማህበራዊ አገልግሎታቸዉን ያበረክታሉ፡፡

  4. ማንኛዉም እድሜዉ ለትምህርት የደረሰ ልጅ ሁሉ ወደ ትምህርት ቤት በመሄድ አስፈላጊዉን ዕዉቀት በመገብየት ለተሻለ ሕይወት ይዘጋጃል፡፡

  5. የመጓጓዣ መንገዶችና መስመሮች በአገር ዉስጥ በሰፊዉ ተዘርግቶ ህዝቡ ሁሉ እንደልብ ከከተማ ከተማ ከአገር አገር ወደ ዉጭም ጨምሮ እንዲዘዋወር ዕድሉ ይኖረዋል ፡፡

  6. ዘመናዊ የኮሚኒኬሽን ቴክኖሎጂም ተዘርግቶ ለማንኛዉም ህዝብ እንዲጠቀምበትና ገደብና ችግር እንዳይሆነዉ ተመጣጣኝ ባለ ዋጋ ይቀርባል፡፡

  7. አገር ዉስጥ ያሉት የቋንቋ የባህል የዘር የሃይማኖት ዓይነቶች ብዛት የአገር ጸጋና ኩራት በመሆናቸው ሁሉም ተከብረዉና አስፈላጊዉ ድጋፍ እየተደረገላቸዉ እንዲዳብሩ ይደረጋል፡፡ልዩነቶችን የመከፋፈል የመጣላት የመዋጋት ምክንያት መሆኑ ቀርቶ የአንድነት የመከባበር የመተሳሰብ ምክንያት ናቸዉ፡፡

  8. የመንግስት ሰራተኞችም አዋቂ አስተዋይ ባለሙያ በመሆናቸው ተግባራቸዉን በሙሉ መድሎ ጉቦ በሌለበት በሥነ ሥርዓትና በቅልጥፍና ያከናውናሉ፡፡ የሚከፈላቸዉና ለኑሮአቸዉ ተመጣጣኝ በመሆኑ ለግል ጥቅማቸዉ ሳይሉ ህዝቡን ሁሉ በእኩልነትና በስነ ስርዓት ያስተናግዳሉ፡፡

  9. የአካባቢዉ ንብረት ጥበቃም ከመቼውም ይበልጥ መዳበር ይዟል፡፡አፈሩ እየተሸረሸረ መሄድ ቆሟል፡፡ ጫካዎች መመንጠራቸዉ ከመቆሙም በላይ በፊት የተመነጠሩት አዲስ ዛፎች ተተክለዉባቸው የተፈጥሮ እንሰሳትና አዕዋፋት እየተመለሱ ይታያሉ፡፡

  10. የአገሪቱ የተፈጥሮ ጸጋ እየተመለሰ ስለመጣና በተለያዩ ቦታዎች ጎብኞዎች የሚስብ የዕንግዳ ማስተናገጃዎች በሰፊዉ በመዘርጋታቸዉ ከዓለም ዙሪያ በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠሩ ቱሪስቶችን እየተቀበለች ታስተናግዳለች፡፡ ይህም ለአገሪቱ ኢኮኖሚ ከፍተኛ ገቢ በማስገኘት ላይ ይገኛል፡፡

bottom of page