top of page

መሐንዲሳዊ  አሰራር

4ኢፒር - መሐንዲሳዊ ምርት ማጎልመስ 

 

 4ኢፒር ሰፊና ሁሉን ያጠቃለለ ፈጣን የልማት መንገድ ነዉ። በመመሪያዎች እና በዝርዝር በቀረቡት ተሞክሮዎች በመከተል ታዳጊ አገሮች ራሳቸዉን ችለዉ ምርት በማጎልመስ ህዝቦቻቸዉ የተሟላ ኑሮና የዕድገት ደረጃ እንዲደርሱ መንገዱን ያሳያሉ፡፡ ይህንንም የሚቀዳጁት የተፈጥሮን የአካባቢን ሁኔታ በመጠበቅና በመንከባከብ ስለሆነ ዉጤቱ ለአልም ሕዝብ በሙሉ ጠቃሚ ነዉ፡፡ ሕዝቦች ወደታቀደዉ የምርት ደረጃ መድረስ የሚችሉት ግንዛቤና የዕዉቀት ደረጃ በማሳደግ፤ በልዩ ልዩ የስራ መስክ ገብተዉ እንዲሰሩ የሚያስችላቸዉን እዉቀት በድርጊት በመቅሰም፤ ለዚህም እተለያዩ ቀልጣፋ የትምህርት ፕሮግራሞች በመሳተፍ፤ ብሎም ምርታቸዉን በማሳደግ መሆኑን ያሳያል፡፡

 

የ4ኢፒር ፕሮግራሞች በመሐንዲሳዊ መንገድ የተዋቀሩት ዋናዉ ማክንያት የተዉሰበሰቡና የተቆላለፉት የኢኮኖሚ፤ የህብረተሰብ፤ የቴክኒክ፤ የአካባቢ መበላሸትና የመሳሰሉትና ችግሮች ደረጃ በደረጃ በተጨባጭ በመፍታት መልስ ስለሚያስገኝ ነዉ። በተጨማሪም የችግሮች ሁሉ ዋና ስረ መንስኤ ሆነው ሕዝብን በችግር አስሮ ያሉት ዋና ሁለት ምክንያቶች (፩ኛ) ሕዝቡ ቴክኖሎጂን ለመጠቀም ባለመቻሉና (፪ኛ) ምርትን ሊያሻሻል ወይም ሊያሳድግ ባለመቻሉ ናቸው፡፡ መሐንዲሣዊ አሰራር እነዚህን ችግሮች በተቀናጀ መንገድ ለመፍታት ያስችላል፡፡

 

መሐንዲሳዊ አሰራር ማለት ተጨባጭና በድርጊት የሚታዩ ርምጃዎችን በማካሄድ፤ ተሞክረዉ በተደጋጋሚ ጥሩ ዉጤት ያስገኙ መርሃ ግብሮችንና እስታንዳርዶችን በመከተል፤ የተተለሙት ግቦች ዘንድ በአስተማማኝና በተሻለ ዋስትና ሊያደርስ የሚያስችል አሰራር ነዉ፡፡መሐንዲሳዊዉ አሰራር የ4ኢፕር ዋና አካል ሆኖ የቀረበዉ ለረጅም ጊዜ ብዙ የኢኮኖሚ ዕድገቶችን በመመርመርና በማጥፋት፤ በትንሽ ጀምረዉ ከፍተኛ ደረጃ የደረሱ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችን ዕድገት በመመርመር፤ ብሎም ግሩም ድንቅና አስደናቂ የሆኑ በልዩ ልዩ ዓለም የተከናወኑ ግዙፍ ወይም ሜጋ ፕሮጀከቶችን መርሆና ተመክሮ በመከተል ነዉ፡፡ በተጨማሪ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ሁኔታ በቀጥተኛና ምንም አይነት ተጽዕኖ በሌለበት አመለካከት በመመርመር ከአለፉት አርባ ዓመታት እስካሁን የተደረጉ ሥራዎችን፤ ሙከራዎች፤ ዉጤቶችና ተሞክሮዎች በመገንዘብ ከዚያም በመጀመር ነዉ፡፡

ተመክሮዎች

 

በአሁኑ ጊዜ አለምን እየከፋፈሉና እያለያዩ የሚገኙት ነገሮች በሶስት አበይት መደቦች ሊከፈሉ ይችላሉ፡፡ እነዚህም የዕዉቀት ደረጃና ግንዛቤ፤ የኢኮኖሚ ሁኔታ እና የተፈጥሮ ሀብት መንከባከብ ናቸዉ፡፡እነዚህ ሶስት ነገሮች በሙሉ በስነ ሥርዓት የጠበቀ የአለም ክፍል ወይም አገር ሕዝቡም ደስታ የመላበትና የሰላም የጤና ሕይወት ይኖራል፡፡ አንዱን ወይም ሁለቱን ያጎደለ ሕብረተሰብ ከፍተኛ ችግር ይገጥመዋል፡፡ የተጓደሉት ወይም ያልተሟሉት ነገሮች ጊዜአቸውን ጠብቀዉ በመፈንዳት ከፍተኛ ጥፋት ያደርሳሉ ዓለምም በልዩ ልዩ መንገድ አንድ ቦታ የተቀሰቀሰዉ መዘዝ ወይም ጥፋት ለሌሎችም በመተላለፍ የዓለምን ጸጥታና ጤና ያቃዉሳል፡፡

 

4ኢፒርን ልዩ አሰራር የሚያደርገዉ አሰራሩ በአለም ላይ ሊሰሩ ሊታሰቡ ይቅር ሊሞከሩ የማይችሉ የሰዉ ልጆች ደረጃ በደረጃ ሠርተዉ የጨረሷቸዉ ተደናቂና ተዓምራዊ ሜጋ ፕሮግራሞችን መርሆ በመያዝ ነዉ፡፡ እንደምሳሌም የሚጠቀሱ ድንቅ ስራዎች እንደላሊበላ ቤተክርስቲያኖች ሥራ፤ እንግሊዝንና ፈረንሳዊያን ከባህር ሥር የሚያገናኘዉ የባቡር መንገድ፤ ከ 600 ሰዉ በላይ ሰዉ ጭኖ ዉቅያኖስ አቆርጦ የሚበረዉ አዉሮፕላን አሰራር፤ ቻይና በአምስት ዓመታት ዉስጥ ከአምስት ሚሊዮን ሕዝብ በላይ የሚኖርበት ሁሉን ነገር ያካተተ ከተማ ሠርቶ ህዝቡ ከገጠር ወጥቶ እንዲኖርበት የተደረጉት ውጤቶች ናቸዉ፡፡

 

ከዚህ ጋር የተያያዘ ዋና መንስኤዉ ግን ኢትዮጵያ ዉስጥ እየተደጋገመ በየጥቂት ዓመታት እየመጣ ብዙ ሕዝብ እየጨረሰ የሚያልፈዉን የረሃብና ድርቅ ችግር ለመፍታት ያልተቆረጠ የረዥም ጊዜ ጥናት ነዉ፡፡ እንደዚህ ዓይነቱ የሰዎች እንደቅጠል መርገፍ ለማንም ሰዉ የሚዘገንነዉ ጉዳዩ ስለሆነ በበለጠ ለመዘጋጀትና ጉዳቱን ለማቆም የሁሉም ሰው ትብብርና አብሮ መነሳት ቅድሚያ የሚሰጠዉ ጉዳይ ስለሆነ ነዉ፡፡

bottom of page