top of page

የማምረት ቅልጥፍና ሲጨምር 

ችግርና ስቃይ ይጠፋና ሰላምና ደስታ ይሰፍናል

ሠላምና ጸጥታ

ሰዎች የማይመረጥ ምርጫ ላይ የሚደርሱት የሚሞክሩትና የሚሰሩት ሁሉ ውጤት ሳያስገኝ ነው። ህጻናትና ዕናቶች ንጹህ ያልሆነ ውሓ እየጠጡ እንደቅጠል ሲረግፉ ፤ የሚችሉትን ሁሉ ሰርተው ውጤታቸው ረሃብ ችግርና ስቃይን ማቆም ሳይችል ሲቀር፤ ሁሉን ርግፍ አርገው አገር ለቀው በርሃ ጥሰው ወደ ማይፈልጉት ወደ የማይቀበላቸው አገር ይሰደዳሉ።. ይህም ጠብ ግርግር አደጋ ጦርነት ሰላም መደፍረስ ያመጣል። 

 

እታዳጊ አገሮች የማምረትን ቅልጥፍና ማሳደግ አማራጭ የሌለው፡ አፋጣኝ ዕድገት የሚያስገኝ፤  ችግርን ስቃይን ማስወገጃ፤ አካባቢን ጠብቆ መያዣና ዘላቂ ሰላምና ማስፈኛ መነገድ ነው። የማምረት ቅልጥፍና የሚያመለክተው አንድ ሰው በተወሰነ ጊዜ ውስጥ የማምረት ችሎታውን ነው። ለምሳኤ እንደ ኢትዮጵያ አሉ አገሮች የማምረት ቅልጥፍናው በቀን ፩ ዶላር ሲያስገኘው እለሙ ወይም ዕበለፀጉ አገሮች ያለ ሰራተኛ የማምረት ቅልጥፍናው ዝቅተኛው ደረጃ በቀን ከ፹ እስከ መቶ ዶላር ያስገኘዋል።  በቀን ፩ ዶላር ብቻ አገኝቶ ሰው የሚፈልጋቸውን ዕቃወች ገዝቶና አገልግሎቶችን አግኝቶ መኖር አይችልም። በተለይም የዓለም ገብያ ለሁሉም ሰው ክፍት በሆነበት ጊዜ በቀን አንድ ዶላር የሰራና በቀን ምቶ የሰራ አበረው መገብየት አይችሉም። ትንሽ የሰራው በችግር መሰቃየቱ ይቀጥላል ማለት ነው። ይህ ሁኔታ ከቀጠለ በምጀምሪያ አገር ውስጥ ፀጥታ ይደፈርሳል ክዚያም ቀስ በቀስ ዓለም ዙሪያ የዳረሳል።  . 

 

አሁን በልጽገው የሚገኙት የአውሮፓ አገሮች ለበዙ መቶ ዓመታት ሰዋጉና ሲጨፋጨፉ የኖሩት ለሃብት ቅሚያና ንጥቂያ ነበር። ሰላምና ፀጥታ ሰፍኖ በመተባበርና ሕብረት እየመሰረቱ ያሉት የማምረት ቅልጥፍናቸውን በኢንዱስትሪና በምርምር በጣም ስላሳደጉ ነው። ስለዚህ ሰላምን ለማግኝትና ከችግር ለመውጣት ዓይነተኛው መንገድ ምርትን ማሳደግ መሆኑን የሚያሳዩ አሥር ምክንያቶች ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል

አስሩ ምክንያቶች

የማምረትን ቅልጥፍና  መጨመርና ማሳደግ እያንዳንዱን ሰው የሚከተሉትን እንዲያከናውን ይረዳዋል 

  1. በየትም ቦታ እንደሚኖር እንደማንኛውም ሰው የማወቅ፤ የመማር፤ የመፍጠር፤ የማምረት፤ የመዝናናት፤ አዲስ ነገር የማውጣት ያማረ ህብረት መመስረት ከትናንት ዛሬ የተሻለ ደረጃ መድረስ 

  2. ጊዜያቸውን ዕውቀታቸውን ሃይላቸውን ተጠቅመው የላቁ የበረከቱ ያማሩ ዕቃዎችን ሰርቶ አገልግሎቶችን አሻሽሎ አበርክቶና ተበርክቶ በየቀኑ ማደግ 

  3. የገቢ ምንጫቸው በየቀኑ እያደገና እየተሻሻለ መምጣት

  4. ከትናንት ዛሬ ጤናማ ደስተኛ እየሆነ ለረዥም እድሜ መብቃት

  5. ልጆቹን የልጅልጆቹን ዘመዶቹን ረድቶና ተንከባከቦ ያማረ ኑሮ መኖር 

  6. በሌላ ቦታ ወይም በሌላ ዓለም ላሉ ህዝቦች ረድቶ ከጊይዛዊ ችግራቸው ተካፍሎ  

  7. ዕንስሣትን አጽዋትን ወንዞችን ተራሮችን ጫካዎችን እና ማንኛወንም ነገር ጠብቆና ተንከባክቦ መያዝ  

  8. በለምለም በንፁህና በተሻሻለ አካባቢ ያለምንም አደጋ በደስታ መኖር 

  9. ለሚቀጥለው ትውልድ ያማረና የተሻሻለ የተፈጥሮ ሃበት ትቶ ማለፍ 

  10. ከላይ የተዘረዘሩትን ሁሉ ለማግኘት ለማድረገ መመኘት ዕቅድ ግብ ማውጣት ብሎም በመትጋት እንዲፈፀሙ ያላቁዋረጠ ጥረት ማድረግ ናቸው።  

መጥፎ ዉሃ ጠጥተው በብዛት የሚያልቁት ሕጻናት ናቸው

እነዚህ ሰእሎች በአጋጣሚ የተነሱ ሳይሆን በአብዛኛው አገር እየተፈፀመ ያለ ነው። ከ፷ በመቶ በላይ በተበታተኑ ገጠር መንደሮች የሚኖረው ሕዝብ ንፁህ ውሃ የለውም።.በዚህም የተነሳ ነው ብዙ ህዝብ የመያለቀው የሰውምም ዕድሜ አጭር የሆነው።  የአብዛኛዎች በሽታ መንሴ የተበላሸ ውሃ መጠጣት መሆኑ ታወቇል።  

bottom of page